የመጨረሻዋ ስዓት !!

" የመጨረሻዋ ስዓት !! "
" ከእያንዳንዱ ብርሀን ጀርባ ጨለማ እንዳለ አስተውል፡፡ ያለህበት ብርሀን ዘላቂ ይሆንልህ ዘንድ መልካም ነገሮችን ብቻ አድርግ፡፡
ክፋት ካከልክበት ከጨለማው ስር ትወድቅና ታሪክ በበጎ አያነሳህም
ከአለባቸው ደሳለኝ አበሻ (ለንደ)
የሰማንያ ዓመት ዕውቀትን ለመገብየት ግድ ሰማንያ ዓመት መኖር የለብንም ። ሰማንያ ዓመት ከኖሩት በትሕትና መጠየቅ ወይንም የታሪክ ድርሳናትን መፈተሽ ይገባናል ።
የአለማችን ታላላቅ ሰዎች ፀሀይ ስታዘቀዝቅባቸው፣ ጀንበር ሳትጠልቅባቸው በፊት የዚችን ከንቱ ዓለም የመጨረሻዋ ስአት ላይ የሚገርም ስንብት ያደርጋሉ :: ይህ ታሪክ ሲፈፀም ላላዩት ላልሰሙት ታሪክ ምስክርነቱን ሊሰጥ ዛሬ በፊታችሁ ቆሟል ::
ካነበብኩት አንድ ለመንገድ ልበላችሁ
ታላቁ አሌክሳንደር በህይወት ዘመኑ ብዙ መንግስታትንና ሀገሮችን በቁጥጥሩ ስር ያደረገ ጀግና ንጉስ ነበር፡፡ አንድ ጊዜ ብዙ ሀገራትን ድል አድርጎ ወደሃገሩ እየተመለሰ ሳለ በጣም አመመዉ፡፡
የኔ የሚላቸዉ ጀኔራሎቹንና ቁልፍ ሰዎችም እንዲያርፍና ህክምና እንዲከታተል ማድረግ ጀመሩ፡፡ ነገር ግን የሱ ህመም ከቀን ወደቀን እየባሰና ወደሞት አፋፍ እየቀረበ መጣ፡፡
አንድ ቀን ግን ህመሙ እጅግ ከብዶ በመምጣቱ አሌክሳንደር እንደማይድን አዉቆታል፡፡ ጄነራሎቹን ሁሉ አስጠርቶ ኑዛዜ መናዘዝ ጀመረ... “ስሙኝ...ከደቂቃ በኋላ ወደማልመለስበት እሄዳለሁ ነገር ግን ስሞት ሶስት ነገሮች እንድታደርጉልኝ እፈልጋለሁ አላቸዉ፡፡
• የመጀመሪያዉ የመቃብር ሳጥኔ እኔን ሲያክሙኝ የነበሩ ዶክተሮች ብቻ ተሸክመዉ ወስደዉ እንዲቀብሩኝ
• ሁለተኛዉ ወደ መቀበሪያዬ ቦታ የሚወስደዉ መንገድ በወርቅና በከበረ ድንጋይ እንዲሰራ
• ሶስተኛዉ ደግሞ ሁለቱም እጆቼ ከመቃብር ሳጥኑ ዉጪ እንዲታዩ አዝዣለሁ ብሎ የመጨረሻዎቹን ትንፋሾች መሳብ ጀመረ፡፡
የንግግሩን ግራ አጋቢነት የከበቡት ዶክተሮችና አገልጋዬች ባይረዱትም ንጉስ ነዉና ሁሉም ዝም ብለዉ እሺታቸዉን ገለፁ፡፡ ነገር ግን በዚህ ግራ የገባዉ የቅርቡ ጀነራል ንጉሱን እንደምንም ብሎ ጠየቀው
“ንጉስ ሆይ ሶስቱ ኑዛዜህ አልገባኝምና እባክህ ቢቻልህ ምን ማለት እንደሆነ ብትነግረኝ?” ንጉሱም እንዲህ አለዉ
“ሁሉም ሰዉ እንዲያዉቅልኝ የምፈልገዉ ሶስት ወሳኝ ነገር አለ፡፡
ልክ እንደ መጀመሪያዉ ኑዛዜ ሰዉ የፈለገዉን ያህል ህክምናና እንክብካቤ ቢደረግለት ከሞት አያመልጥም፡፡ ሁሉም ዶክተሮች ሞትን አሸንፈዉ ህመምተኛዉን ሰዉ ሊያስጥሉት ፈፅሞ አይችሉም!
እንዲያዉ ለጊዜዉ ይሞክራሉ እንጂ ዞሮ ዞሮ ሁሉም ወደሞት ነዉ!
ሁለተኛዉ ደግሞ በህይወት ዘመኔ ስዳክርለትና ስደክምለት የኖርኩት ሃብት አሁን ይዤዉ መሄድ አልችልም፡፡ ገንዘብንና ሀብትን እያሳደዱ መኖር ከንቱና ባዶ የማይጠቅም መሆኑን ተረዳሁ፡፡
ሶስተኛዉ ደግሞ ወደዚህ አለም ስመጣ በባዶዬ መጥቻለዉ፣ ስሄድም እንዲሁ በባዶዬ! ምንም ሳልይዝ እጄ ባዶ እንደሆነ ነዉ፡፡
የእናንተም እጣ እንዲሁ ነዉ በባዶህ እንደመጣህ ድምቡሎ ሳትይዝ በባዶህ ትመለሳለህ” አለዉ ይባላል ፡፡
ውድ የፌስ ቡክ ወዳጆቼ
የሰው ልጆች ስንባል ነገ ሁሉንም ጥለነው ባዶቻችንን ወደ መቃብር
ለምንሔደው አለም ለለ መረዳዳት የሚያጨካክነን ነገር ምንድ ነው ? ::
ለሀገራችን ሌላ ታሪክ መስራት ቢያቅተን እንኳን በሐገራችን ጅምላ ጨራሽ የኮረና ወረርሽኝ ለመከላከል ለሚደረገው የወገን አድን ዘመቻ ያለችንን ለማካፈል አንጨካከን :: በመከራ ቀን የኢትዮጵያን ልጆች አንርሳ ፤ የዛሬ ሰው ብቻ አንሁን ፤ የትላንቱንም እናስብ፤ አንገት የተፈጠረው ዞሮ ለማየት ነውና ።ሰምቶ ማመን ፣ ከተጎዱት መማር አስተዋይነት መሆኑን አንርሳ ። የሰማንያ ዓመት ዕውቀትን ለመገብየት ግድ ሰማንያ ዓመት መኖር የለብንም ። ሰማንያ ዓመት ከኖሩት በትሕትና መጠየቅ ይገባናል ።
ለማንኛውም ልብ ያለው ልብ ይበል ::
ጮማዬን ደብቄ ብቻዬን ልበላው
ጣፋጩን እርጎዬን ሸሽጌ ልጠጣው
ድርቡን ሸማዬን ደብቄ ልለብሰው
ደሀ ጎረቤቴን ምንም እንዳያምረው
"ቸግሮኛል"አልኩት ለአፌም የምቀምሰው
ጮማዬን ሸሽጌ ማጦቴን ስነግረው
ደሀ ጎረቤቴን እንባ ተናነቀው
"እኔ ብሎኝ " አዝኖ ከቤት እደወጣ
ሽምብራውን ይዞ ሊያካፍለኝ መጣ።
ድሀ ቆራጡ ::
እኔም ለዛሬው በዚሁ አበቃሁ በሌላ ዝግጅት እስክንገናኝ ቸር ይግጠመን ::
አለባቸው ደሳለኝ አበሻ (ለንደን፣)
Sign in or sign up to post comments.
Be the first to comment

Related Articles

Latest Articles

Most Popular