" ይህ ወቅት የሰዎችን ነፍስ የሚፈትን ወቅት ነው " ! !
ከአለባቸው ደሳለኝ አበሻ ( ለንደን)
በፈረንሳይ አብዮት ውስጥ ያለፈው ቶማስ ፔይን ነበር ለአርእስት የተጠቀምኩትን አባባል በአንድ ወቅት የፃፈው: :
"ይህ ወቅት የሰዎችን ነፍስ የሚፈትን ወቅት ነው: : ሐቅና ውሸት ሕዝባዊነትና ግለኝነት ጀግንነትና ፍርሐት እበላባይነትና መስዋእትነት በከፍተኛ ደረጃ በውስጣችን ጦርነት የሚያካሒዱበት ነው: :
በፍፁምነትና በህዝባዊ በጎነት ታላቅ እምነት ያለው መንፈሳዊ ስርአት ያስፈልገናል " ነበር ያለው ::
ውድየፌስቡክ ወዳጆቼ
ለአንድ ሕዝብ እድገትና ልማት መሰረታዊ ግባዕቶች የሐገር መረጋጋት ቅድሚያ የሚሰጠው አማራጭ የለለው ጉዳይ ነው:
ፓለቲካው ካልሰከነና ከጦዘ ሰላም አይኖርም ሰላም ማለት ደግሞ የትጥቅ ፍልሚያ አለመኖሩና የተኩስ ድምፅ አለመሰማት ብቻ ተደርጎ መወሰድ የለበትም: : የሰላም መስፈን የሚታወቀው ስጋት ሲጠፋ ብቻ ነው ነገርግ አሁን ያለንበት ሁኔታ ግን የእያንዳንዳችንን ነፍስ የሚፈትን ወቅት ነው: :
ዛሬ በሐገራችን ባህርዳርና በአዲስ አበባ ላይ የተፈፀመው ትልቅ ብሔራዊ አደጋ ዝም ብለን እንደ ከዚህ ቀደሙ አድበስብሰን የአንድ ሳምንት ቁጭትና የሾሻል ሚዲያ ጫጫታ ብቻ አድርገን ማለፍ የሚኖርብን አይመስለኝም ::
ለሞቱት ጀግና የኢትዮጵያ ልጆች ፍትህ እንዲያገኙ በሕብረት ሁነን መጠየቅ ይኖርብናል ??
ጉዳዩ የሐገር ሕልውና ጉዳይ ስለሆነ የክፍፍል የአሻጥር ፓለቲካ የህዝባችንን የመንፈስ ጥንካሬ በእጅጉ እየጎዳው በመሆኑ መንግስት የኢትዮጵያን ህዝብ ዕድል ወዴት እንደሚያመራ ለማወቅ ውስብስብና አስቸጋሪ ቢሆንበትም በአስቸኳይ መፍትሔ መፈለግ ይኖርበታል:: ቤተሰቦቻቸው በግፍ ለተገደሉባቸው ወላጅ አልባ ለሆኑት የሟች ቤተሰቦችና ልጆች ሕዝብና መንግስት ከጎናቸው ሊቆምላቸው ይገባል ::
በተጨማሪም.በአማራ ክልል ባህርዳርና በአድስ አበባ ላይ ለተፈጠረው ግድያ ተጠያቂ ናቸው የሚባሉትን ወንጀለኞች በመንግስት አካላት ብቻ ሳይሆን በገለልተኛ አካላትም ጭምር ወንጀሉ እንዲጣራ ቢደረግ መንግስት ከሀሜትና ከአሉባልታ ባለፈ በኢትዮጵያ ህዝብ ትልቅ አመኔታና ክብር ያገኛል ብየ እገምታለሁ: :
ውድየፌስ ቡክ ወዳጆቼ ለመሆኑ በእርግጠኝነት እነዚህን ጥያቄዎች በግል ለራሳችሁ ጠይቃችሁ መልስ አግኝታችሁ ታውቃላችሁ ወይ? : :
ለምንድነው የኢትዮጵያ ህዝብ ሰላምና አንድነት ተግባራዊ ለማድረግ ስንጥር ሙከራችን ሁሉ የሚከሽፍብን? ..............
ለአንድነታችን ጧት ማታ ስንደክም ህልማችን እውን እንዳይሆን የሚፈልጉት ዋነኞቹ የፀረ ኢትዮጵያ ተዋንያኖች እነማናቸው ? ብለን እውነተኛ ታሪክ ፀሐፊዎችን ጠይቀን የምናውቀው ስንቶቻችን ነን ?::
እኔ እንደሚገባኝ. ግን ኢትዮጵያን ሌትና ከቀን በመረባረብ ለማጥፋት እየሰሩ ያሉ ግለሰቦችና ቡድኖች እነማናቸው ብሎ በብሔራዊ ደህነት በኩል ማጣራትና ማወቅ የመንግስት ሐላፊነትና ተግባር ቢሆንም እንደ አንድ ዜጋ እራሳችሁን ጠይቃችሁ ከወዳጆቻችሁ ጋር ተነጋግራችሁበት ታውቃላችህ ዎይ ?
ይህ ካልሆነ ደግሞ በሐገራችን ችግር ላይ ጥናትና ምርምር በሞያተኞች አስጠንተን ችግራችንን በቅጡ አውቀን በማያዳግም ሁኔታ መፍትሔ በአስቸኳይ ማግኜት ይኖርብናል ብላችችሁ አስባችሁበት ታውቃላችሁ ወይ ? : :........
እንግዲህ እነዚህን ጥያቄዎች በማንሳት እስኪ እንወያይበት! !
በሌላም በኩል ደግሞ ምን አይነት ስልትና ዘዴ መጠቀም አለብን ?
የሚሉ ወሳኝ ጥያቄዎች እንደ አንድ ዜጋም እንደመንግስትም በጋራ መመለስ. እና መፍትሔ መፈለግ ይኖርብናል ብየ አምናለሁ ?
በበኩሌ እንደ አንድ መፍትሔ የሚመስለኝ ፣ በየ አካባቢው አስተዋይ ልቦና ያላቸው ፣ ለወገንና ለአካባቢው ደህንነት ፣ አሳቢና ተቆርቋሪ ብዙ ሰዎች እንዳሉ እገምታለሁ : :
ስለዚህ በልተጨበጠ መረጃ በሶሻል ሚዲያ ላይ ከምንጫጫ ከነዚህ ወገኖች ጋር በመወያየት የሐገራችን ሰላም በአስተማማኝ ሁኔታ ለማስፈን ጊዚያችንን ጉልበታችንን ሐብታችንን ለሐገር ግንባታ ለማዋል እንችል ዘንድ እስካሁን ያልሞከርናቸውን ስልት መፈልግ ይኖርብናል: :
በአንፃሩም ችግራችንን ማወቅ ግማሽ መፍትሔ ስለሚሆን ትክክለኛውን መፍትሔ ቁርጥ አድርገን መወሰን ይኖርብናል: : ካለበለዚያ የውሳኔ እጥረት የጀግኖች ሞት ይሆናል: :
እንደኔ አስተሳሰብ ቢሆን የምመርጠው በቅድሚያ ህገመንግስታችንን መፈተሽና. የቋንቋ ፌደራሊዝምን አርቀን መቅበር ይኖርብናል: :
ምክኒያቱም ፣ ከምርጫ በፊት ብሔራዊ እርቅ ለሐገራችን ስለሚያስፈልጋት : :
የብሔረሰብ ፖለቲካ ለአንዴየና ለመጨረሻ ግዜ እትዮጵያ ውስጥ ሞቶ መቀበር አለበት :: በታሪክ ለአንድም ሐገር ሲጠቅም አልታየም: :
በዚህ ምክንያት ዛሬ ኢትዮጵዊያነት ከፍተኛ አደጋ ላይ ወድቋል: :
ስለዚህ ሁላችንም አድስ የአንድነት ስሜት መፍጠር የሚያስችል መመሪያ በማውጣት ብሔራዊ ጠቀሜታ ባለው ሀሳብ ላይ በየ ክልሉ ያሉ መሪዎች ሁሉ መስማማት ይኖርባቸዋል: :
ከዚህ በዘለለ የሰውን ልጅ የሚክል ክብር ነገር በከንቱ ማጥፋት በምንም መመዘኛ ተቀባይነት የለውም: :
የሰው ልጅ የተፈጠረው በአምላክ መልክ በመሆኑ የምድራችን እጅግ ክብር ነገር ነው
ስለዚህ ሰውን መግደል የምድራችንን እጅግ ክቡርና ቅዱስ የሆነ ነገር ማጥፋት በመሆኑ
በእምነትም በምሐበራዊ ሳይንስም በታሪክም የተወገዘ መጥፎ ተግባር ነው: :
ሆኖም ግን ስለ ሌላው ደኅንነት ምንም ደንታ የሌላቸው ዓመጸኛ ሰዎች የራስ ወዳድነት ፍላጎታቸውን ለማሳካት ሲሉ የበርካታ ሰዎችን ሕይወት በጭካኔ ይቀጥፋሉ። የሰው ሕይወት ማለት የማይተካና የማይመለስ በመሆኑ ፣ እንደ ተሰባሪ ዕቃ ነው፤ የሚቆጠረው: : ይህ ድርጊት የሚፈፀመው በእርግጥ በኛ ሐገር ብቻ ሳይሆን በአለማችን ላይም በእያንዳንዱ ቀን በአማካይ ከ160,000 በላይ ሰዎች ይሞታሉ!
በየዓመቱ 59 ሚሊዮን ያህል ሰዎች እንደሚሞቱ የሚገመት ሲሆን በሒሳብ ስሌት እንኳን ብናሰላው በእያንዳንዱ ሴኮንድ በአማካይ 2 ሰው ይሞታል ማለት ነው።
በእያንዳንዱ 102 ሴኮንድ ውስጥ አንድ ሰው በጦርነት ምክንያት ይሞታል።
▪ በእያንዳንዱ 61 ሴኮንድ ውስጥ አንድ ሰው ይገደላል።
▪ በእያንዳንዱ 39 ሴኮንድ ውስጥ አንድ ሰው ራሱን ይገድላል።
▪ በእያንዳንዱ 26 ሴኮንድ ውስጥ አንድ ሰው በመኪና አደጋ ምክንያት ይሞታል።
▪ በእያንዳንዱ ሦስት ሴኮንድ ውስጥ አንድ ሰው ከረሀብ ጋር በተያያዘ ምክንያት ይሞታል።
▪ በእያንዳንዱ ሦስት ሴኮንድ ውስጥ አምስት ዓመት ያልሞላው አንድ ሕፃን ይሞታል።
ብዙ ነገር ማለት ይቻላል :: ሞት አዲስ ነገር ሆኖ አንገት ሊያስደፋንና ካሰብንበት አላማ ፍፁም ሊገታን አይችልም ::
ግን ለምን በከንቱ. ወንድም ለወንድም እንገዳደላለን: : ይህ በእርግጥ ያስቆጫል: : ከህዝባችን የተቆርቋሪነት ስሜትና ከሐገራችን ፍቅር ስንነሳ እርስ በእርስ በመገዳደል ሳይሆን ለወደፊቱ የተፈጠሩትን ልዩነቶች ሰከን ብለን በክብ ጠረንጴዛ ዙሪያ መፍታት የምንችልበት አቅም መገንባት ያስፈልገናል ::
" ይህ ወቅት የሰዎችን ነፍስ የሚፈትን ወቅት " በመሆኑ እጅ ለእጅ ተያይዘን በጋራ መቆም ይኖርብናል: :
ለዛሬው በዚሁ አበቃሁ በሌላ ዝግጅት እስክንገናኝ
"ጆሮ ያለው ይስማ " ቸር ይግጠመን! !
አለባቸው ደሳለኝ አበሻ. ( ለንደን )
ሸር በማድረገዎት ደስ ብሎኛል